በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለ1

የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት

ይሖዋ አምላክ የመግዛት መብት አለው። የእሱ አገዛዝ ከሁሉ የተሻለ ነው። ለምድርና ለሰው ልጆች ያለው ዓላማ ፍጻሜውን ያገኛል።

4026 ዓ.ዓ. በኋላ

‘እባቡ’ በይሖዋ የመግዛት መብትና አገዛዝ ላይ ጥያቄ አስነሳ። ይሖዋም የእባቡን ይኸውም የሰይጣንን ራስ የሚጨፈልቅ “ዘር” እንደሚያስነሳ ቃል ገባ። (ዘፍጥረት 3:1-5, 15) ሆኖም ይሖዋ ለተወሰነ ጊዜ ሰዎች በሰይጣን ተጽዕኖ ሥር ሆነው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ፈቀደ።

1943 ዓ.ዓ.

ይሖዋ ለአብርሃም ተስፋ የተደረገበት ዘር በእሱ የዘር ሐረግ በኩል እንደሚመጣ ነገረው።–⁠ዘፍጥረት 22:18

ከ1070 ዓ.ዓ. በኋላ

ይሖዋ ለንጉሥ ዳዊት፣ ቆየት ብሎ ደግሞ ለልጁ ለሰለሞን ተስፋ የተደረገበት “ዘር” በእነሱ የዘር ሐረግ በኩል እንደሚመጣ አረጋገጠላቸው።–⁠2 ሳሙኤል 7:12, 16፤ 1 ነገሥት 9:3-5፤ ኢሳይያስ 9:6, 7

29 ዓ.ም.

ይሖዋ፣ የዳዊትን ዙፋን የሚወርሰው ተስፋ የተደረገበት “ዘር” ኢየሱስ መሆኑን አስታወቀ።–⁠ገላትያ 3:16፤ ሉቃስ 1:31-33፤ 3:21, 22

33 ዓ.ም.

እባቡ ይኸውም ሰይጣን፣ ኢየሱስን በማስገደል ተስፋ የተሰጠበትን “ዘር” ተረከዝ አቁስሏል። ይሁንና ይሖዋ ኢየሱስን ከሞት በማስነሳት በሰማይ ሕይወት የሰጠው ከመሆኑም ሌላ ፍጹም ሕይወቱን መሥዋዕት በማድረግ የከፈለውን ዋጋ ተቀብሎታል፤ ይህም የአዳምን ዘሮች ኃጢአት ይቅር ለማለትና ለእነሱ የዘላለም ሕይወት ለመስጠት መሠረት ሆኖ ያገለግላል።–⁠ዘፍጥረት 3:15፤ የሐዋርያት ሥራ 2:32-36፤ 1 ቆሮንቶስ 15:21, 22

በ1914 ዓ.ም. ገደማ

ኢየሱስ እባቡን ይኸውም ሰይጣንን ወደ ምድር በመወርወር እንቅስቃሴው በምድር ላይ ብቻ እንዲወሰን አድርጓል።–⁠ራእይ 12:7-9, 12

ወደፊት

ኢየሱስ ሰይጣንን ለ1,000 ዓመት ካሰረው በኋላ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያጠፋዋል፤ በምሳሌያዊ አነጋገር ራሱን ይጨፈልቀዋል። ይሖዋ ለምድርም ሆነ ለሰው ልጆች ያወጣው የመጀመሪያ ዓላማ ፍጻሜውን ያገኛል፤ ስሙ ከነቀፋ ነፃ ይሆናል፤ እንዲሁም የአገዛዙ ትክክለኝነት ይረጋገጣል።–⁠ራእይ 20:1-3, 10፤ 21:3, 4