በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 4, 2017 ዓ.ም. (ሚያዝያ 12, 2025)

የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ ያከብራሉ፤ ይህም ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው፦ “ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት።”—ሉቃስ 22:19

በዚህ ፕሮግራም ላይ እንድትገኝ በአክብሮት ጋብዘንሃል።

ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች

ፕሮግራሙ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

አንድ ሰዓት ገደማ።

ፕሮግራሙ የሚካሄደው የት ነው?

በአካባቢህ ስለሚካሄድበት ቦታ መረጃ እንዲሰጡህ የይሖዋ ምሥክሮችን አነጋግር።

መግቢያ በነፃ ነው?

አዎ።

ሙዳየ ምጽዋት ይዞራል?

አይዞርም።

ለፕሮግራሙ ምን ዓይነት ልብስ ልልበስ?

የይሖዋ ምሥክሮች ለፕሮግራሙ የአለባበስ ሕግ አላወጡም፤ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ልከኝነትና አክብሮት የሚንጸባረቅበት አለባበስ እንዲኖራቸው የሚሰጠውን ምክር ይታዘዛሉ። (1 ጢሞቴዎስ 2:9) ውድ ልብስ ወይም የፕሮግራም ልብስ ለብሰህ መምጣት አይጠበቅብህም።

በመታሰቢያው በዓል ላይ ምን ይከናወናል?

ስብሰባው የሚጀምረውና የሚደመደመው በመዝሙርና አንድ የይሖዋ ምሥክር አገልጋይ በሚያቀርበው ጸሎት ነው። ኢየሱስ የሞተው ለምን እንደሆነ እንዲሁም አምላክና ክርስቶስ ያደረጉልን ነገር ምን ጥቅም እንደሚያስገኝልን የሚያብራራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንግግር ይቀርባል።

መጪዎቹ የመታሰቢያው በዓላት የሚከበሩት መቼ ነው?

2017 ዓ.ም. (2025)፦ ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 4 (ሚያዝያ 12)

2018 ዓ.ም. (2026)፦ ሐሙስ፣ መጋቢት 24 (ሚያዝያ 2)