በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ

4 | ተስፋህ

4 | ተስፋህ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የዓለም ቀውስ የሚፈጥረው ጭንቀት በሰዎች ጤንነትም ሆነ ስሜት ላይ ትልቅ ጫና ያሳድራል። እነዚህ ነገሮች ተጽዕኖ ያሳደሩባቸው ሰዎች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ አይኖራቸውም። ታዲያ ለችግራቸው ምን ምላሽ ይሰጣሉ?

  • አንዳንዶች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ጨርሶ ማሰብ አይፈልጉም።

  • ሌሎች በመጠጥ ወይም በዕፆች ከችግራቸው ለመደበቅ ይሞክራሉ።

  • ጥቂቶች በሕይወት መኖር ምንም ጥቅም የለውም ብለው ይደመድማሉ። ‘ሞቼ ብገላገልስ?’ ብለው ያስባሉ።

ማወቅ ያለብህ ነገር

  • ዛሬ ያሉብህ አንዳንድ ችግሮች ጊዜያዊ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ባልጠበቅኸው መንገድ ነገሮች ይሻሻሉ ይሆናል።

  • ያለህበት ሁኔታ ባይቀየርም እንኳ ችግርህን ለመቋቋም ማድረግ የምትችላቸው ነገሮች አሉ።

  • መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ተስፋ ይሰጣል፤ ይህ ተስፋ የሰው ልጆች ችግሮች ለዘለቄታው እንደሚወገዱ ይገልጻል።

አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ስለ ነገ ፈጽሞ አትጨነቁ፤ ምክንያቱም ነገ የራሱ የሆኑ የሚያስጨንቁ ነገሮች አሉት። እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ በቂ ችግር አለው።”—ማቴዎስ 6:34

ስለ ነገ አትጨነቅ። እንዲህ ማድረግ የዛሬውን ኃላፊነትህን በአግባቡ እንዳትወጣ እንቅፋት ይሆንብሃል።

እንዲህ ቢሆንስ እያሉ መጥፎ መጥፎውን ማሰብ ውጥረት ከመጨመርና ተስፋን ከማጨለም ውጭ ሌላ ጥቅም የለውም።

መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ተስፋ ይሰጣል

አንድ ጥንታዊ ዘማሪ ወደ አምላክ ሲጸልይ እንዲህ ብሏል፦ “ቃልህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።” (መዝሙር 119:105) ታዲያ የአምላክ ቃል ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያበራልን እንዴት ነው?

ጨለማ ውስጥ ስንጓዝ መብራት መያዛችን የት መርገጥ እንዳለብን ለማወቅ ይረዳናል። መጽሐፍ ቅዱስም እንደዚህ መብራት ነው፤ ከባድ ውሳኔ ማድረግ ሲያስፈልገን አቅጣጫችንን እንድናውቅ ይመራናል።

ብርሃን በመንገዳችን ላይ በርቀት ያለውን ነገርም አሻግረን እንድናይ ይረዳናል። መጽሐፍ ቅዱስም በተመሳሳይ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብሩህ ተስፋ እንዲኖረን ይረዳናል።