በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከውጥረት እፎይታ ማግኘት

ከውጥረት ነፃ የሆነ ሕይወት መምራት ትችላለህ

ከውጥረት ነፃ የሆነ ሕይወት መምራት ትችላለህ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ ያዘለ ምክር አላስፈላጊ ውጥረትን ለማስወገድ ይረዳናል። ሆኖም ውጥረት የሚፈጥሩ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እንደማንችል የታወቀ ነው። ፈጣሪያችን ግን ይችላል። በመሆኑም እኛን እንዲረዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስን ሾሞልናል። ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ሰው ሆኖ ምድር ላይ በኖረበት ወቅት ካከናወናቸው ነገሮች የሚበልጡ አስደናቂ ነገሮችን በቅርቡ በመላው ዓለም ያከናውናል። ለምሳሌ፦

ኢየሱስ ምድር ሳለ እንዳደረገው የታመሙትን ይፈውሳል።

“ሰዎችም በተለያየ በሽታና ከባድ ሕመም የሚሠቃዩትን . . . ሁሉ ወደ እሱ አመጡ፤ እሱም ፈወሳቸው።”—ማቴዎስ 4:24

ኢየሱስ ሁሉም ሰው መኖሪያ ቤትና በቂ ምግብ እንዲያገኝ ያደርጋል።

“[የክርስቶስ ተገዢዎች] ቤቶችን ይሠራሉ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ ወይንንም ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። እነሱ በሠሩት ቤት ሌላ ሰው አይኖርም፤ እነሱ የተከሉትንም ሌላ ሰው አይበላውም።”—ኢሳይያስ 65:21, 22

የኢየሱስ አገዛዝ በመላው ዓለም ሰላምና ደህንነት ያሰፍናል።

“በእሱ ዘመን ጻድቅ ይለመልማል፤ ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ሰላም ይበዛል። ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተገዢዎች ይኖሩታል። . . . ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።”—መዝሙር 72:7-9

ኢየሱስ የፍትሕ መጓደልን ያስወግዳል።

“ለችግረኛውና ለድሃው ያዝናል፤ የድሆችንም ሕይወት ያድናል። ከጭቆናና ከግፍ ይታደጋቸዋል።”—መዝሙር 72:13, 14

ኢየሱስ መከራን እና ሞትን ሳይቀር ያስወግዳል።

“ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”—ራእይ 21:4