በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት የሌና ኮዤቭኒኮቫ

መጋቢት 6, 2024
ሩሲያ

እህት የሌና ኮዤቭኒኮቫ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደባት

እህት የሌና ኮዤቭኒኮቫ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደባት

መጋቢት 4, 2024 በሰማረ ክልል በቶልያቲ የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት የሌና ኮዤቭኒኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል። የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለየሌናም ሆነ ስደት እየደረሰባቸው ላሉት ሌሎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘በመንፈሱ አማካኝነት ኃይል’ በመስጠት ጸሎታችንን ስለሚመልስልን አመስጋኞች ነን።​—ኤፌሶን 3:16

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 15, 2023

    የወንጀል ክስ ተመሠረተ

  2. ግንቦት 16, 2023

    ቤቷ ተፈተሸ

  3. ግንቦት 18, 2023

    የጉዞ ገደብ ተጣለባት

  4. ነሐሴ 16, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  5. መጋቢት 4, 2024

    ጥፋተኛ ነች ተብላ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደባት

a እህት ኮዤቭኒኮቫ ሐሳብ የሰጠችው ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ነው።