በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ዬሌና ዩሬንኮቫ

የካቲት 21, 2024 | የታደሰው፦ መጋቢት 25, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | በሚያበረታቱ ወንድሞችና እህቶች ተከብቤያለሁ

ወቅታዊ መረጃ—እህት ተፈረደባት | በሚያበረታቱ ወንድሞችና እህቶች ተከብቤያለሁ

መጋቢት 22, 2024 የቶልያቲ ማዕከላዊ የአውራጃ ፍርድ ቤት፣ እህት ዬሌና ዩሬንኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል፤ የሁለት ዓመት የገደብ እስራትም ፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋን ‘እጅ ለእጅ ተያይዘን እያገለገልን’ ባለንበት በዚህ ወቅት እሱ ዬሌናንም ሆነ ስደትን በጽናት እየተጋፈጡ ያሉትን ሁሉ በፍቅሩ እየተንከባከበ በመሆኑ አመስጋኞች ነን።​—ሶፎንያስ 3:9

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 15, 2023

    የክስ ፋይል ተከፈተባት

  2. ግንቦት 16, 2023

    ቤቷ ተፈተሸ። ምርመራ ከተደረገባት በኋላ የጉዞ ገደብ ተጣለባት

  3. ሰኔ 5, 2023

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባት

  4. ነሐሴ 23, 2023

    ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ