ግንቦት 29, 2023
ሩሲያ
ወንድሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እገዛ ስደትን ተጋፍጠዋል
በፕሪሞርስኪ የሚገኘው የፖዣርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ኒኮላይ ዲኽትያር፣ በወንድም አንድሬ ልያኾቭ፣ በወንድም ዩሪ ፖኖማሬንኮ እና በወንድም ኦሌግ ሰርጌዬቭ ክስ ላይ በቅርቡ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
አጭር መግለጫ
ከኒኮላይ፣ ከአንድሬ፣ ከኦሌግ እና ከዩሪ ሁኔታ እንደምንማረው የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረጋችን “ለማንኛውም መልካም ሥራ . . . ሙሉ በሙሉ ብቁ” ያደርገናል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 16, 2021
ዩሪ ላይ የክስ ፋይል ተከፈተበት። የተጠረጠረው “የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አስተባብረሃል” በሚል ወንጀል ነው
ሐምሌ 22, 2021
የዩሪ መኖሪያ ቤት ተፈተሸ
ሐምሌ 24, 2021
ዩሪ የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት
ኅዳር 1, 2021
የኦሌግ መኖሪያ ቤት ተፈተሸ
ኅዳር 2, 2021
ኦሌግ የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት
የካቲት 12, 2022
ኦሌግ በክስ መዝገቡ ውስጥ ተካተተ
መጋቢት 14, 2022
ኒኮላይ በክስ መዝገቡ ውስጥ ተካተተ
መጋቢት 15, 2022
አንድሬ በክስ መዝገቡ ውስጥ ተካተተ
ነሐሴ 10, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ