በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 24, 2019
ኢኳዶር

ጉዋያኪል፣ ኢኳዶር—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ጉዋያኪል፣ ኢኳዶር—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከሰኔ 14-16, 2019

  • ቦታ፦ ኤስታዲዮ ሞንዩሜንታል ባንኮ ፒቺንቻህ፣ ጉዋያኪል፣ ኢኳዶር

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ የኢኳዶር ምልክት ቋንቋ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 53,055

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 702

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,300

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ማዕከላዊ አሜሪካ፣ ምያንማር፣ ሞልዶቫ፣ ስፔን፣ ቤልጅየም፣ ቦሊቪያ፣ አርጀንቲና፣ ኩባ፣ ካዛክስታን፣ ኮሎምቢያ፣ ኮሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ፖላንድ

  • ተሞክሮ፦ የስታዲየሙ ባለቤት የሆነው የባርሴሎና የስፖርት ክለብ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሆሴ ፍራንሲስኮ ሲቫዮስ እንዲህ ብለዋል፦ “ዘንድሮም ሆነ ባለፉት ዓመታት ባደረጋችኋቸው ስብሰባዎች ላይ ምንም ችግር አጋጥሞን አያውቅም። መልካም ባሕርይ እንዳላችሁና የተደራጃችሁ እንደሆናችሁ ከስብሰባዎቻችሁ በግልጽ ማየት ችለናል። ቀላል ባይሆንም እንኳ ሁሌም ለስብሰባዎቻችሁ ጥሩ ዝግጅት ታደርጋላችሁ እንዲሁም በደንብ የተደራጃችሁ ናችሁ። የተማራችሁ፣ መልካም ምግባር ያላችሁና የተደራጃችሁ ጥሩ ሰዎች ናችሁ። የትኛውም ከተማ አልፎ ተርፎም የትኛውም አገር እናንተን እንዲያስተናግድ እናበረታታለን።”

 

የኢኳዶርን ቤቴል እየጎበኙ ያሉ ልዑካን ፎቶግራፍ ሲነሱ

በአካባቢው ያሉ ወንድሞችና እህቶች ከልዑካኑ ጋር ሲያገለግሉ

ከተለያዩ አገራት የመጡ ልዑካን በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን ላይ በኅብረት ሲዘምሩ

በስብሰባው ላይ ከተጠመቁት 702 ወንድሞችና እህቶች መካከል የተወሰኑት

ልዑካኑ ስብሰባው ላይ ማስታወሻ ሲጽፉ

ልዑካኑ፣ ኮሪያውያን ፍቅርን ለማመልከት የሚጠቀሙበትን ምልክት በእጃቸው ሲያሳዩ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ኬነዝ ኩክ የቅዳሜን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ

ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በስብሰባው የመጨረሻ ቀን ላይ ሕዝቡን ሲሰናበቱ

የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ልዑካኑን በተለያዩ ትርዒቶች ሲያዝናኑ