በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 28, 2022
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት በኪፔንዴ ቋንቋ ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት በኪፔንዴ ቋንቋ ወጣ

የካቲት 20, 2022 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በኪፔንዴ ቋንቋ ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱ የተገለጸው አስቀድሞ በተቀዳ ፕሮግራም አማካኝነት ነው። የኮንጎ (ኪንሻሳ) ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ኒኮላስ ሃይፊንገር መጽሐፍ ቅዱሱ በኤሌክትሮኒክ ቅጂ መውጣቱን 10,000 ገደማ ለሚሆኑ አስፋፊዎች አሳወቀ። ከሚያዝያ 2022 ጀምሮ የታተመውን ቅጂ ማግኘት ይቻላል።

የይሖዋ ምሥክሮች ታሪክ በኪፔንዴ ቋንቋ ተናጋሪዎች ክልል ውስጥ የጀመረው በ1960ዎቹ ማካንዳ ማዲንጋ ሄንሪ የተባለ ሰው አንድ የመጠበቂያ ግንብ እትም በደረሰው ወቅት ነው። በጽሑፉ ላይ ያነበበውን ነገር ካሰበበት በኋላ ያነበበው መረጃ እውነት መሆኑን ስላመነበት የተማረውን ነገር ለሌሎችም ለማካፈል ወሰነ። ከጊዜ በኋላ ተጠምቆ የይሖዋ ምሥክር ሆነ። ከዚያም በ1979 ኪዬፉ ውስጥ በኪፔንዴ ቋንቋ የመጀመሪያው ጉባኤ ተቋቋመ።

በኪንሻሳ ካለው ቅርንጫፍ ቢሮ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በኪክዊት ያለው የኪፔንዴ ቋንቋ የርቀት ትርጉም ቢሮ

ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የግል ጥናት ሲያደርጉም ሆነ ምሥራቹን ሲሰብኩ ትልቅ እገዛ ያደርግላቸዋል። ለምሳሌ ወንድም ሃይፊንገር አዲስ የወጣው መጽሐፍ ቅዱስ “ትክክለኛ እና ግልጽ” እንደሆነ እንዲሁም “የይሖዋን ስም በበኩረ ጽሑፉ ላይ በነበረባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ መልሶ እንዳካተተ” ተናግሯል።

ይህ አዲስ ዓለም ትርጉም ወንድሞቻችን ‘ፍሬ ማፍራታቸውንና ስለ አምላክ ትክክለኛ እውቀት በመቅሰም ማደጋቸውን’ እንዲቀጥሉ እንዲረዳቸው እንጸልያለን።—ቆላስይስ 1:10