“የሕይወት መጽሐፍ” ውስጥ የተጻፈው የእነማን ስም ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
“የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል” እና “የመታሰቢያ መጽሐፍ” ተብሎ የተጠራው ‘የሕይወት መጽሐፍ’ የዘላለም ሕይወት የሚያገኙ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይዟል። (ራእይ 3:5፤ 20:12፤ ሚልክያስ 3:16) አምላክ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚጻፈው ማን እንደሆነ የሚወስነው ለእሱ ያሳዩትን ታማኝነት መሠረት በማድረግ ነው።—ዮሐንስ 3:16፤ 1 ዮሐንስ 5:3
አምላክ የሰው ዘር “ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ” የታማኝ አገልጋዮቹን ስም በመጽሐፍ ላይ የመጻፍ ያህል በአእምሮው ውስጥ ይዟል። (ራእይ 17:8) ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው የመጀመሪያው ታማኝ ሰው አቤል ሳይሆን አይቀርም። (ዕብራውያን 11:4) ይሖዋ ’የእሱ የሆኑትን የሚያውቅ’ አፍቃሪ አምላክ ስለሆነ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈሩ ሰዎችን በስም ብቻ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ እያንዳንዳቸውን ያውቃቸዋል።—2 ጢሞቴዎስ 2:19፤ 1 ዮሐንስ 4:8
አንድ ሰው ስሙ “ከሕይወት መጽሐፍ” ላይ ሊደመሰስ ይችላል?
አዎ። አምላክ በጥንቷ እስራኤል የነበሩ ታዛዥ ያልሆኑ ሰዎችን አስመልክቶ “የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ” በማለት ተናግሯል። (ዘፀአት 32:33) ታማኝ መሆናችንን ካስመሠከርን ግን ‘ከሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል’ ላይ ስማችን አይደመሰስም።—ራእይ 20:12