በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው?

 ብዙ ሰዎች መስቀል በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚኖሩ ክርስቲያኖች መለያ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እኛ የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቲያኖች ብንሆንም መስቀልን ለአምልኮ አንጠቀምበትም። ለምን?

 አንደኛው ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የሞተው የመስቀል ቅርጽ ባለው እንጨት ላይ ሳይሆን በአንድ ወጥ እንጨት ላይ እንደሆነ ስለሚናገር ነው። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ለክርስቲያኖች “ከጣዖት አምልኮ ሽሹ” የሚል ጠንካራ ማሳሰቢያ ይሰጣል። ይህ ደግሞ መስቀልን ለአምልኮ መጠቀምን ይጨምራል።​—1 ቆሮንቶስ 10:14፤ 1 ዮሐንስ 5:21

 ኢየሱስ “በመካከላችሁ ፍቅር ካለ ሰዎች ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ” ማለቱ ትኩረት የሚስብ ነው። (ዮሐንስ 13:34, 35) ኢየሱስ ይህን በማለት፣ እውነተኛ ተከታዮቹ ተለይተው የሚታወቁት የራስን ጥቅም መሥዋዕት የሚያደርግ ፍቅር በማሳየት እንጂ በመስቀል ወይም በሌላ በማንኛውም ዓይነት ምስል እንዳልሆነ ግልጽ አድርጓል።