በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች የተደራጁት እንዴት ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች የተደራጁት እንዴት ነው?

 እያንዳንዱ ጉባኤ የሚመራው በሽማግሌዎች አካል ነው። ሃያ ገደማ የሚሆኑ ጉባኤዎች አንድ ወረዳ ይመሠርታሉ፤ አሥር የሚሆኑ ወረዳዎች ደግሞ በአንድ አውራጃ ሥር ይታቀፋሉ። ሁሉም ጉባኤዎች ፕሮግራም ወጥቶላቸው የወረዳ የበላይ ተመልካችና የአውራጃ የበላይ ተመልካች ተብለው በሚጠሩ ተጓዝ ሽማግሌዎች ይጎበኛሉ።

 ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በዎርዊክ፣ ኒው ዮርክ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት የሚያገለግሉ በእምነቱ ውስጥ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮችን ያቀፈው የበላይ አካል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችንና ትምህርቶችን ይሰጣል።​—የሐዋርያት ሥራ 15:23-29፤ 1 ጢሞቴዎስ 3:1-7