በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

ለንባብ በሚያመች መንገድ ማስተካከል—አንድሮይድ

ለንባብ በሚያመች መንገድ ማስተካከል—አንድሮይድ

JW Library፣ በምታነብበት ወቅት ልትጠቀምባቸው የምትችል በርካታ ገጽታዎች አሉት። እነዚህ ገጽታዎች አንድን ርዕስ ወይም ምዕራፍ ለማንበብ ስትከፍት በስክሪኑ አናት በስተቀኝ በኩል ይወጣሉ።

ከእነዚህ ገጽታዎች መካከል አንዳንዶቹን ለማግኘት ሌሎች የሚለውን ቁልፍ መጫን ሊያስፈልግህ ይችላል።

ለንባብ በሚያመች መንገድ ማስተካከል የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ እነዚህን መመሪያዎች ተከተል፦

 ቋንቋ መቀየር

እያነበብክ ያለውን ምዕራፍ ወይም ርዕስ በሌላ ቋንቋም ማንበብ ትችላለህ።

  • ቋንቋዎች የሚለውን ስትጫን የምታነብበው ጽሑፍ የሚገኝባቸውን ቋንቋዎች ዝርዝር በሙሉ ማየት ትችላለህ። በዝርዝሩ ውስጥ ከላይ የሚታዩት አዘውትረህ የምትጠቀምባቸው ቋንቋዎች ናቸው። ቀለል ባለ ቋንቋ የተዘጋጁ የመጠበቂያ ግንብ እትሞችንም እዚሁ ማግኘት ትችላለህ። የምትፈልገውን ቋንቋ ስም በመጻፍም ቋንቋውን ማግኘት ትችላለህ።

  • ያላወረድካቸው ቋንቋዎች የደመና ምልክት ይታይባቸዋል። ጽሑፉን ለማውረድ ቋንቋውን ተጫን። ጽሑፉን ስታወርድ የደመናው ምልክት ይጠፋል። ያወረድከውን ጽሑፍ ለማንበብ ቋንቋውን ተጫን።

 የፊደል መጠን ማስተካከል

የጽሑፉን መጠን፣ ለማንበብ በሚያመችህ መንገድ ማስተካከል ትችላለህ።

የፊደል መጠን ማስተካከያ የሚለውን ቁልፍ ተጫን፤ ከዚያም የፊደል መጠን ማስተካከያውን በማንቀሳቀስ የጽሑፉን መጠን መቀነስ ወይም መጨመር ትችላለህ። የምታደርገው ማስተካከያ አፕሊኬሽኑ ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም ጽሑፎች የፊደል መጠን ይቀይረዋል።

 ምስል ወይም ጽሑፍ ማየት

አንዳንድ ጽሑፎችን በምስል ወይም በጽሑፍ መልክ ማየት ይቻላል። የምትፈልገውን ቁልፍ በመጫን ከአንዱ ወደ ሌላው መቀያየር ትችላለህ።

  • ምስል አሳይ፦ ምስል አሳይ የሚለው ምርጫ ጽሑፉ ሲታተም የሚኖረውን ገጽታ ያሳያል። አንዳንዶች እንደ መዝሙር መጽሐፍ ያሉ ጽሑፎችን በምስል መልክ ማየትን ሊመርጡ ይችላሉ፤ ምክንያቱም ይህን ማድረጋቸው የሙዚቃ ኖታውን እንዲያዩ ያስችላቸዋል።

  • ጽሑፍ አሳይ፦ ጽሑፍ አሳይ የሚለው ምርጫ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በሊንክ መልክ ያስቀምጣል፤ ሊንኩን ስትጫን በመረጥከው የፊደል መጠን ጥቅሱን ያወጣልሃል።

 መክፈቻ ምረጥ

መክፈቻ ምረጥ የሚለው ገጽታ በJW Library ላይ የሚገኙትን ነገሮች በሌሎች አፕሊኬሽኖች ለመክፈት ያስችልሃል።

መክፈቻ ምረጥ የሚለውን ቁልፍ ስትጫን የተለያዩ መክፈቻዎችን ያስመርጥሃል። ለምሳሌ በኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት ክፈት የሚለውን ቁልፍ ስትጫን እያነበብክ ያለውን ጽሑፍ በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት ላይ ይከፍትልሃል።

 መጽሐፍ ቅዱሶችን እንደምትፈልገው ማስተካከል

በአንድ ጽሑፍ ውስጥ የሚገኝን ጥቅስ ስትጫን ጥቅሱ በተለያዩ ትርጉሞች ይወጣል። ካወረድካቸው መጽሐፍ ቅዱሶች መካከል ጥቅሱን ማየት የምትፈልግባቸውን ትርጉሞች ለመምረጥ እንደምትፈልገው አስተካክል የሚለውን ተጫን።

የመደመር ወይም የመቀነስ ምልክቶቹን በመጫን አንድን ትርጉም ዝርዝሩ ውስጥ መጨመር ወይም ከዚያ ውስጥ መቀነስ ትችላለህ። የዝርዝሩን ቅደም ተከተል ለማስተካከል አንድን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ላይ ወደ ታች አንቀሳቅስ።

JW Library ላይ ተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሶችን የምታገኝበትን መንገድ ለማወቅ “መጽሐፍ ቅዱሶችን ማውረድና መጠቀም—አንድሮይድ” የሚለውን ተመልከት።

እነዚህ ገጽታዎች የወጡት የካቲት 2015 JW Library 1.4 ሲወጣ ነው፤ አንድሮይድ 2.3 ወይም ከዚያ በላይ ለሚጠቀሙ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Libraryን መጠቀም ጀምር—አንድሮይድ” የሚለውን ከፍተህ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ርዕስ ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።