በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

JW Libraryን መጠቀም ጀምር—አንድሮይድ

JW Libraryን መጠቀም ጀምር—አንድሮይድ

JW Libraryን ለመጠቀም በመምረጥህ ደስ ብሎናል። ይህ አፕሊኬሽን የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለማጥናት እንዲረዳህ ነው። የአፕሊኬሽኑን ዋና ዋና ገጽታዎች ለማግኘት ዋናውን ማውጫ መጠቀም ትችላለህ። ዋናውን ማውጫ ለማግኘት ስክሪኑን ከግራ ወደ ቀኝ አንሸራት ወይም በስተግራ አናት ላይ ያለውን የማውጫ ምልክት ተጫን።

 መጽሐፍ ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ክፍል የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ለማንበብና ለመጫን ያስችልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ የመጽሐፉን ስም ከዚያም ምዕራፉን ተጫን። በምታነብበት ወቅት የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ የኅዳግ ማጣቀሻዎችንና አቻ ትርጉሞችን በማጥኛ ሣጥኑ ውስጥ መመልከት ትችላለህ።

ሌላ ጥቅስ ማውጣት ከፈለግክ ዋናውን ማውጫ በመክፈት መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን እንደገና ተጫን፤ በዚህ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን ዝርዝር ታገኛለህ።

 የሕትመት ውጤቶች

የሕትመት ውጤቶች በሚለው ክፍል ውስጥ የተለያዩ ጽሑፎችን እንዲሁም የኦዲዮና የቪዲዮ ፕሮግራሞችን ታገኛለህ። የምትፈልገውን ጽሑፍ ለማንበብ መጀመሪያ ጽሑፉን ከዚያም ርዕሱን ተጫን። በምታነብበት ወቅት ጥቅሶቹንም ማየት ትችላለህ። ጥቅሱን ስትጫነው በማጥኛ ሣጥኑ ውስጥ ይከፈትልሃል። በማጥኛ ሣጥኑ ውስጥ ያለውን ሊንክ ስትጫን ጥቅሱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይወጣልሃል።

ሌላ ጽሑፍ መክፈት ከፈለግክ ዋናውን ማውጫ በመክፈት የሕትመት ውጤቶች የሚለውን በድጋሚ ተጫን፤ ይህም ወደ ሕትመት ውጤቶቹ ዝርዝር ይወስድሃል።

 የዕለት ጥቅስ

የዕለቱን ጥቅስ ለማየት፣ ዋናውን ማውጫ ከፍተህ የዕለት ጥቅስ የሚለውን ተጫን።

 ኢንተርኔት

በዋናው ማውጫ ውስጥ በሚገኘው ኢንተርኔት በሚለው ክፍል ውስጥ ወደ ድረ ገጾቻችን የሚወስዱ ሊንኮች ይገኛሉ።

 አዳዲስ ገጽታዎች

በJW Library ላይ ያሉትን አዳዲስ ገጽታዎች በሙሉ ለማግኘት የምትጠቀምበትን መሣሪያ በየጊዜው ማደስ ያስፈልግሃል።

ለምትጠቀምበት መሣሪያ የሚሆን አዲስ ስሪት በመጣ ቁጥር ያንን መጫኑ የተሻለ ነው። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ተመልከት፦ https://support.google.com/nexus/answer/4457705

በምትጠቀምበት መሣሪያ ላይ ያለውን ማስተካከያ በመጠቀም ወደፊት አዳዲስ ነገሮች በመጡ ቁጥር ያለምንም ጥያቄ እንዲካተቱልህ ማድረግ ትችላለህ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ተመልከት፦ https://support.google.com/googleplay/answer/113412