በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሐዘን ለደረሰባቸው የሚሆን እርዳታ

ሐዘን ለደረሰባቸው የሚሆን የላቀ ማጽናኛ

ሐዘን ለደረሰባቸው የሚሆን የላቀ ማጽናኛ

የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት ስለሚያስከትለው ሐዘን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሰፊ ጥናት ሲደረግ ቆይቷል። ሆኖም ቀደም ብለን እንደተመለከትነው የተሻለ የሚባለው የባለሙያዎች ምክር፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኘው ጠቃሚ ሐሳብ ጋር ብዙውን ጊዜ ይስማማል። ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ዘመን የማይሽረው መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ይሁንና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው፣ እምነት የሚጣልበት ምክር ብቻ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የትም ቦታ የማይገኙና ሐዘን ለደረሰባቸው ሰዎች የላቀ ማጽናኛ የሚሰጡ ሐሳቦችን ይዟል።

  • በሞት ያጣናቸው የምንወዳቸው ሰዎች እየተሠቃዩ እንዳልሆኑ የሚያሳይ ማረጋገጫ

    መጽሐፍ ቅዱስ በመክብብ 9:5 ላይ “ሙታን . . . ምንም አያውቁም” በማለት ይናገራል። በተጨማሪም ‘ሐሳባቸው ሁሉ ይጠፋል’ ይላል። (መዝሙር 146:4) ከዚህም ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን ሰላማዊ ከሆነ እንቅልፍ ጋር ያመሳስለዋል።—ዮሐንስ 11:11

  • አፍቃሪ በሆነ አምላክ ማመን የሚያስገኘው ማጽናኛ

    መጽሐፍ ቅዱስ በመዝሙር 34:15 ላይ “የይሖዋ * ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉ፤ ጆሮዎቹም እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትን ጩኸት ይሰማሉ” በማለት ይናገራል። ስሜታችንን አውጥተን በጸሎት ለአምላክ መግለጻችን ሥቃያችንን ከማስታገስ ወይም ሐሳባችንን ከማረጋጋት የበለጠ ጥቅም አለው። ጸሎት፣ እኛን ለማጽናናት ኃይሉን መጠቀም ከሚችለው ፈጣሪያችን ጋር የግል ዝምድና ለመመሥረት ይረዳናል።

  • ወደፊት የተሻለ ሕይወት እንደሚመጣ የሚገልጽ ተስፋ

    በመቃብር ያሉ ሁሉ ወደፊት ከሞት ተነስተው በምድር ላይ የሚኖሩበትን ጊዜ በዓይነ ሕሊናህ ለመመልከት ሞክር! መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለ ጊዜ እንደሚመጣ በተደጋጋሚ ይናገራል። በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚኖር መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጽ አምላክ “እንባን ሁሉ [ከዓይናችን] ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም” ይላል።—ራእይ 21:3, 4

በይሖዋ አምላክ የሚያምኑ ብዙ ሰዎች፣ በሞት ያጧቸውን የሚወዷቸውን ሰዎች እንደገና እንደሚያዩአቸው የሚገልጸውን ተስፋ በማመናቸው ሐዘናቸውን መቋቋም ችለዋል። ለምሳሌ ያህል፣ ለ65 ዓመታት አብሯት የኖረውን የትዳር ጓደኛዋን በሞት ያጣችው አን እንዲህ ትላለች፦ “የምንወዳቸው ሰዎች ቢሞቱም እየተሠቃዩ እንዳልሆነና አምላክ በመታሰቢያ መቃብር ውስጥ ያሉትን ሙታን በሙሉ እንደሚያስነሳ መጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ ሰጥቶኛል። ባሌን በሞት እንዳጣሁ በማስብበት ጊዜ፣ እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች ወደ አእምሮዬ ስለሚመጡ የደረሰብኝን ከሁሉ የከፋ ሐዘን መቋቋም ችያለሁ!”

በእነዚህ ተከታታይ ርዕሶች ውስጥ ቀደም ሲል የተጠቀሰችው ቲና እንዲህ ትላለች፦ “ቲሞ ከሞተበት ቀን ጀምሮ የአምላክ ድጋፍ አልተለየኝም። በሐዘኔ ወቅት ይሖዋ በእጅጉ እንደረዳኝ ይሰማኛል። ደግሞም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የትንሣኤ ተስፋ እውን ሆኖ ይታየኛል። የትንሣኤ ተስፋ፣ ቲሞን እንደገና እስካገኘው ድረስ በጽናት ለመቀጠል ብርታት ይሰጠኛል።”

እነዚህ አስተያየቶች፣ መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ ተስፋ እንደያዘ አጥብቀው የሚያምኑ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ስሜት የሚያስተጋቡ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር እውን ሊሆን እንደማይችል ወይም ምኞት ብቻ እንደሆነ ቢሰማህ እንኳ ምክሮቹና ተስፋዎቹ አስተማማኝ እንደሆኑ የሚያሳየውን ማስረጃ መመርመርህ ጠቃሚ ነው። እንዲህ ስታደርግ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ሐዘን ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሆን የላቀ ማጽናኛ እንደሚሰጥ መገንዘብ ትችላለህ።

ሙታን ስላላቸው ተስፋ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

ከዚህ ርዕስ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ቪዲዮዎች jw.org/am ላይ ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ በሞት ያጣናቸውን የምንወዳቸውን ሰዎች እንደገና የምናገኝበት ጊዜ እንደሚመጣ ተስፋ ይሰጣል

ስንሞት ምን እንሆናለን?

ስንሞት ምን እንሆንለን? መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው ግልጽ መልስ በጣም የሚያጽናና ነው

ላይብረሪ >ቪድዮዎች በሚለው ሥር ተመልከት (ቪዲዮው መጽሐፍ ቅዱስ በሚለው ሥር ይገኛል።)

ምሥራች መስማት ትፈልጋለህ?

መጥፎ ዜናዎች በሞሉበት በዚህ ዓለም ውስጥ ምሥራች ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች >ሰላም እና ደስታ በሚለው ሥር ተመልከት

^ አን.7 መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ የግል ስም ይሖዋ ነው።