መዝሙር 142:1-7

  • ከአሳዳጆቹ እንዲታደገው ያቀረበው ጸሎት

    • “ሸሽቼ ማምለጥ የምችልበት ቦታ የለም” (4)

    • “ያለኸኝ አንተ ብቻ ነህ” (5)

ማስኪል።* ዳዊት ዋሻ ውስጥ በነበረበት ጊዜ+ የዘመረው መዝሙር። ጸሎት። 142  ድምፄን አውጥቼ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ እጣራለሁ፤+ሞገስ እንዲያሳየኝ ይሖዋን እማጸናለሁ።   የሚያሳስበኝን ነገር በፊቱ አፈስሳለሁ፤የውስጤን ጭንቀት በፊቱ እናገራለሁ፤+   መንፈሴ* በውስጤ ሲዝል፣ እሱን እማጸናለሁ። በዚህ ጊዜ ጎዳናዬን ትመለከታለህ።+ በምሄድበት መንገድ ላይበስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ።   ቀኝ እጄን ተመልከት፤ስለ እኔ ግድ የሚሰጠው* ሰው እንደሌለ እይ።+ ሸሽቼ ማምለጥ የምችልበት ቦታ የለም፤+ስለ እኔ* የሚያስብ ማንም የለም።   ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጣራለሁ። ደግሞም “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤+በሕያዋን ምድር ያለኸኝ አንተ ብቻ* ነህ” እላለሁ።   መንፈሴ እጅግ ተደቁሷልና፣እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ። ከእኔ ይልቅ ብርቱ ስለሆኑከሚያሳድዱኝ ሰዎች ታደገኝ።+   ስምህን አወድስ ዘንድከእስር ቤት አውጣኝ።* ደግነት ስለምታሳየኝጻድቃን በዙሪያዬ ይሰብሰቡ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጉልበቴ።”
ቃል በቃል “ለእኔ እውቅና የሚሰጥ።”
ወይም “ስለ ነፍሴ።”
ቃል በቃል “በሕያዋን ምድር ድርሻዬ አንተ ነህ።”
ወይም “ነፍሴን ከእስር ቤት አውጣት።”