ኦሪጅናል መዝሙሮች

ለመንፈሳዊ ውርሻችን ያለንን አድናቆት የሚገልጹ መዝሙሮች።

አሁኑኑ

የአቅኚነት መንፈስ ለሰዎች ፍቅር እንድናሳይ ይገፋፋናል።

ፈገግታ

በአገልግሎታችን ላይም ሆነ ኑሮ በሚወስደን ቦታ ሁሉ ፈገግታ ማሳየት ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

ስብሰባ የሚያስገኘው ደስታ

በትላልቅ ስብሰባዎች ላይ ስንገኝ በዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን ውስጥ ያለውን አንድነትና ፍቅር የመመልከት አጋጣሚ እናገኛለን።

ያ ቀን ይታይህ

በቅርቡ ሁሉ ነገር አዲስ ይሆናል።

እናመስግንህ

ይሖዋ ቅዱስ መንፈሱን በመስጠት፣ የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንድንቋቋም ይረዳናል። ለዚህ ዝግጅት ያለን አድናቆት እሱን በመዝሙር እንድናወድሰው ያነሳሳናል።

ውሳኔ

የግል ውሳኔዎቻችን አገልግሎታችንን እና ሌሎች ሰዎችን የሚነኩት እንዴት እንደሆነ ማሰባችን ጥበብ ነው።

ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ

ወደፊት ስለሚመጣው ገነት ማሰባችን እንድንጸና ይረዳናል።

በእምነት ይሳካል

ጠንካራ እምነት መገንባት ጥረት ይጠይቃል፤ ሆኖም ጥረት ካደረግን ይሖዋ ይባርከናል።

ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ

የይሖዋን ማሳሰቢያዎች እንደምንወድ በንግግራችንም ሆነ በተግባራችን እናሳይ።

እዚያው አልቀርም

ቀደም ሲል ቀናተኛ የይሖዋ አገልጋይ የነበረች ሴት ወደ ጉባኤው ለመመለስ የሚያስችል ኃይል ያገኘችው እንዴት ነው?

ተዋደን እንኑር

ይሖዋ በትዳራችሁ ውስጥ እንዲኖር ከፈቀዳችሁ ጥምረታችሁ ጠንካራ ይሆናል!

አይተወኝም ለብቻዬ

ይሖዋ አምላካችን መቼም ብቻችንን አይተወንም!

ድፍረት ስጠኝ

ይሖዋ የትኛውንም ፈተና መቋቋም እንድንችል ድፍረት ይሰጠናል።

ደፋር እና ብርቱ

እንድንጸና የሚያበረታታን ተወዳጅ መዝሙር።

አንድ ቤተሰብ

የትም ብንሆን አንድ ቤተሰብ ነን።

“መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል”

ከችግሮቻችን ጋር መታገል ቢኖርብንም ለይሖዋ ታማኝ መሆን እንችላለን።

ይሖዋ አብሮን ነው ሁሌም

ይሖዋ ምንጊዜም ሊረዳን ፈቃደኛ ነው።

ያ አዲስ ዘመን

በዓይነ ሕሊናችን የምንስለው ነገር በአስተሳሰባችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህ መዝሙር ስለ አዲሱ ዓለም እንድናስብ ይረዳናል።

ያንተው ትሁን ነፍሴ

ለይሖዋ ያለን ፍቅር ራሳችንን ለእሱ እንድንወስንና እንድንጠመቅ ያነሳሳናል።

ፍቅር ለዘላለም ይኖራል

የይሖዋ ፍቅር ለዘላለም ይኖራል። ደስታና መጽናኛ ይሰጠናል።

ተወው ለሱ

በጭንቀት ስትዋጥ ይሖዋን እንዲረዳህ ለምነው፤ ያጠነክርሃል እንዲሁም ያጽናናሃል።

እንደ ልጆች

ፍቅር በማሳየት ረገድ እንደ ልጆች መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

እርግጠኛ ሁን

ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን ይሖዋ እንደሚወደን እርግጠኛ መሆን እንችላለን።

በነፃ ይቅር እንድል

ስሜትህን የጎዳው ሰው አለ? በደሉን መርሳት ከብዶሃል? በነፃ ይቅር ማለት የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

እንሩጥ

በሕይወት ሩጫ አሸናፊ ለመሆን ጥሩ ውሳኔዎችን አድርግ።

እንጸናለን

ጠንካራ እምነት ለመገንባት ጥራት ያለው ጥሬ ዕቃ ያስፈልጋል።

ውዴ፣ የኔ

የይሖዋ ስጦታ በሆነው በትዳር ተደሰት።

ልቤን እጠብቃለሁ

በይሖዋ እርዳታ፣ ልብህ በሚያስጨንቁ ሐሳቦች እንዳይወጠር በምታደርገው ትግል አሸናፊ መሆን ትችላለህ።

‘ደስ ይበለን’

ለመደሰት የሚያበቁንን ብዙ ምክንያቶች የሚያስታውስ መዝሙር።

አንድ ሕዝብ ሆነናል

ብዙ ችግርና ፈተና ቢያጋጥመንም ምንጊዜም አንድ ሕዝብ ነን።

ጉልበትህን ስጠው ላምላክህ

ጉልበትህን ይሖዋን ለማገልገል ተጠቀምበት። መቼም አይቆጭህም!

የዘላለም ደስታ

ይሖዋ አሁንም ሆነ ለዘላለም ደስታችን ነው።

እይማ

አዲስ ዓለም እንደሚመጣ በሚገልጸው ተስፋ ደስ ይበልህ።

ጊዜ ስጠው ለሱ

ይሖዋን በትጋት ማገልገል ከሁሉ የተሻለ የሕይወት መንገድ ነው።

በእምነት ዓይኔ

አምላክ ወደፊት ለሰው ልጆች የሚሰጣቸው ሕይወት ምን ያህል አስደናቂ እንደሆነ በዓይነ ሕሊናህ ለመሣል ሞክር።

የይሖዋ ቤተሰብ

በዓለም ላይ እውነትን እየፈለጉ ያሉ ሰዎች አሁንም አሉ። ይህ ቪዲዮ፣ እንዲህ ዓይነቶቹን ቅኖች መፈለግህን እንድትቀጥል ያነሳሳሃል።

አንድ ላይ እንጽና

በወንድማማች ማኅበራችን እና በይሖዋ እርዳታ ማንኛውንም ፈተና በጽናት መቋቋም እንችላለን።

ወደ ማን እሄዳለሁ?

የአንድን ታማኝ የይሖዋ አገልጋይ የሕይወት ዘመን እንቃኝ። ዕድሜውን ሁሉ የእረኛውን ድምፅ የሰማው እንዴት ነው?

ይሖዋን ይዤ

በይሖዋ እርዳታ ፍርሃታችንን ማሸነፍ እንችላለን።

እንታረቅ

በደልን መተውና መታረቅ አይሻልም?

ድክመትህ ላይ ንገሥ

ከስህተትህ ተማር እንጂ ተስፋ አትቁረጥ፤ የትናንቱን ትተህ ለነገው ማንነትህ ሥራ።

አልኖርክም ገና!

ዛሬም ሆነ ወደፊት አስደሳችና ትርጉም ያለው ሕይወት አጣጥም!

የናፈቀን ሰላም! (የ2022 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

ዛሬ ሕይወት በመከራ የተሞላ ቢሆንም እውነተኛ ሰላም እንደሚሰፍን አምላክ የገባው ቃል ያጽናናናል።

አቀረበኝ

ያሳለፉት ሕይወት ምንም ይሁን ምን፣ አምላክ ወዳጆቹ መሆን የሚፈልጉ ሰዎችን ሊያቀርባቸው ፈቃደኛ ነው።

‘አይዘገይ ከቶ!’ (የ2023 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

ይሖዋን በትዕግሥት ስትጠባበቅ ታማኝ አገልጋዮቹ የተዉትን ምሳሌ ተከተል።

በእቅፉ

ወደ ይሖዋ ቤት ለመመለስ አሁንም አልረፈደም።

ሁለት ሳንቲም

የቱንም ያህል ትንሽ ቢመስል፣ ይሖዋ መሥዋዕትህን ያደንቃል።

ያውቃል

ይሖዋ እያንዳንዳችንን በግለሰብ ደረጃ ያውቀናል፤ የውስጥ ስሜታችንን ይረዳል።

ሰላም ሲያዜም ፍጥረት

ይሖዋን ማገልገላችን ሰላም ሰጥቶናል።

ዝም አንልም

በይሖዋ ታመን፤ ፍርሃትህን አሸንፈህ መስበክህን ቀጥል።

እተጋለሁ ለእምነቴ

ጥርጣሬ ቤት ሳይሠራ ለእምነትህ ትጋ።

‘ሰላሜ እንደ ወንዝ’

ይሖዋ የሚሰጠው ሰላም እንደ ወንዝ ነው፤ ለዘላለም ሳይቋረጥ ይፈስሳል።

ወንጌል (የ2024 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

ከመጀመሪያው መቶ ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ወንጌል ሲታወጅ ኖሯል፤ ይህ ተልዕኮ፣ በትውልዶች ሁሉ ግለሰቦች በደስታ የተካፈሉበት፣ ብዙ ዋጋ የከፈሉለት እንዲሁም ኢየሱስ ራሱ የሚመራውና በመላእክት የሚደገፍ ክቡር ሥራ ነው።