በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እተጋለሁ ለእምነቴ

እተጋለሁ ለእምነቴ

አውርድ፦

  1. 1. እውነቱ፣ ይሄ ይሆን ወይ መንገዱ? ኧረ የቱ?

    ደግሞ ጠየቀ ይህ ልቤ፤ አይቀር አንዳንዴ፣

    ሙግት ካሳቤ።

    ፈትኖ ማየት ሁሉን የኔው የቤት ሥራ፤

    በ’ጅ ያለ ወርቅ እንዳይሆንብኝ ኋላ፤

    አልልም ችላ።

    (አዝማች)

    እተጋለሁ ለእምነቴ፤

    ቤት ሳይሠራ ጥርጣሬ።

    ቸል አላውቅም በእምነቴ፤

    ’ባክህ አምላኬ፣ አሳካልኝ ጥረቴን።

    እተጋለሁ

    ለእምነቴ፣

    ለእምነቴ።

  2. 2. ይህ ዓለም መራራው ጣፋጭ፣ ጥቁሩ ነጭ፣ ጠፍቷል ውሉ፤

    ራሴን አልሸነግልም፣ አልወድቅም አልልም፣

    አይቀር ልብ ተንኮሉ።

    አያማትርም ዓይኔ ወደ ማታለያ፤

    ደግሞስ በዚህ ዘመን ማን ሊታመን፣

    ካምላኬ ቃል ወዲያ!

    (አዝማች)

    እተጋለሁ ለእምነቴ፤

    ቤት ሳይሠራ ጥርጣሬ።

    ቸል አላውቅም በእምነቴ፤

    ’ባክህ አምላኬ፣ አሳካልኝ ጥረቴን።

    እተጋለሁ

    ለእምነቴ፣

    ለእምነቴ።

    (መሸጋገሪያ)

    ቃሉን ከፍቼ ሳነብ፣ ሳሰላስል፣

    መዝሙር ስሰማ፣ በጨዋታ መሃል፣

    አላጣም መካሪ ሐሳብ፣ ስንቅ የሚሆን

    ለእምነቴ።

    (አዝማች)

    እተጋለሁ ለእምነቴ፤

    ቤት ሳይሠራ ጥርጣሬ።

    ቸል አላውቅም በእምነቴ፤

    እባክህ አምላኬ፣ እርዳኝ ይሳካ ጥረቴ።

    እተጋለሁ፣

    እተጋለሁ፣

    እተጋለሁ፣

    እተጋለሁ፣

    እተጋለሁ፣

    እተጋለሁ።