በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እንደ ልጆች

እንደ ልጆች

አውርድ፦

  1. 1. አስተምሯል ጌታ

    ትሑት እንድንሆን ቀና።

    እንደ ልጆች ሁኑ ብሎ መክሮ፣

    አሳየን ትንሽ ልጅ ጠርቶ።

    እናክብር ሁሉን፣ ትንሽ ትልቁን፣ ሳንለይ አንዱን ካንዱ።

    (አዝማች)

    እንደ ልጆች በንጹሕ ልብ እንዋደድ፤

    ሕፃናት፣ ተንኮል አያውቁም ቶሎ መፍረድ።

    እንደ ልጆች ደጎች እንሁን ለቸገረው፤

    ሕፃናት፣ ልዩነት አያይም ዓይናቸው።

  2. 2. ያ የሕፃናት ለዛ

    ቶሎ ያልፋል እንደዋዛ።

    ፍቅር በሌለው ዓለም ውስጥ አድገው፣

    ክፋት ይማራል ልባቸው።

    ቅድሚያ ለኔ ነው፣ ዓለም የሚለው፤ ብርቅ ሆኗል ትሑት ሰው።

    (አዝማች)

    እንደ ልጆች በንጹሕ ልብ እንዋደድ፤

    ሕፃናት፣ ተንኮል አያውቁም ቶሎ መፍረድ።

    እንደ ልጆች ደጎች እንሁን ለቸገረው፤

    ሕፃናት፣ ልዩነት አያይም ዓይናቸው።

    እንደ ልጅ እንሁን።

    (መሸጋገሪያ)

    ሁሌ ልጅ ሆኖ

    መኖር ባይቻልም፣

    በጊዜ ሂደት

    መብሰል ባይቀርም፣

    ያንን ቅንነት

    ማጣት አንፈልግም፤

    እንደ ልጆች ይሁን ልባችን።

    (አዝማች)

    እንደ ልጆች በንጹሕ ልብ እንዋደድ፤

    ሕፃናት፣ ተንኮል አያውቁም ቶሎ መፍረድ።

    እንደ ልጆች ደጎች እንሁን ለቸገረው፤

    ሕፃናት፣ ልዩነት አያይም ዓይናቸው።

    እንደ ልጅ እንሁን።