በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም

የይሖዋ ምሥክሮች፣ የጤና ችግሮችና የአካል ጉዳተኝነት በሕይወታቸው ደስታና እርካታ ከማግኘት ሊያግዷቸው እንደማይችሉ ተገንዘበዋል።

“ይሖዋ ሕይወታችንን አትርፎልናል”

ሳውባጊያ በጣም ተስፋ ስለቆረጠች የራሷንም ሆነ የልጇን ሕይወት ለማጥፋት አስባ ነበር። ሆኖም ሐሳቧን እንድትቀይርና ሕይወቷ ዓላማ እንዳለው እንዲሰማት የሚያደርግ ነገር አጋጠማት፤ ምን ይሆን?

ፍቅር በተግባር ሲገለጽ አይተዋል

ዓይነ ስውር የሆኑና ብሬይል ማንበብ የማይችሉ ሁለት ወንድማማቾችና እህታቸው ጉባኤው ፍቅራዊ ድጋፍ ስላደረገላቸው መንፈሳዊ እድገት ማድረግ ችለዋል።

ዴዤኔሮ ብራውን፦ ሐዘን ቢሰብረኝም ተስፋው ጠግኖኛል

ይሖዋ በድንገተኛ አደጋ ሐዘን ያጋጠማቸውን አገልጋዮቹን የሚረዳቸው እንዴት ነው?

የጤና እክል ቢኖርባትም ለሌሎች አሳቢነት ታሳያለች

ማሪያ ሉሲያ ማየትና መስማት የተሳናት ብትሆንም ሌሎች መርዳት የቻለችው እንዴት ነው?

በቬኔዙዌላ በአስቸጋሪ ጊዜ ይሖዋን ማገልገል

በቬኔዙዌላ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በአገልግሎት በቅንዓት መካፈላቸውንና አንዳቸው ለሌላው “የብርታት ምንጭ” መሆናቸውን ቀጥለዋል።

የጤና ችግር ሌሎችን ከማጽናናት አላገዳትም

ክሎዲን ስለ ችግሯ እያሰበች መቆዘም አልፈለገችም፤ ስለዚህ ሌሎችን ለማጽናናት አቅም እንዲሰጣት አምላክን ለመነችው።

አስቸጋሪ ሁኔታ ቢያጋጥማትም በጽናት ቀጥላለች

ቨርጂኒያ ላለፉት 23 ዓመታት ያህል፣ ሎክድ ኢን ሲንድሮም በተባለ በሽታ ስትሠቃይ ቆይታለች። ሆኖም ስለ ወደፊቱ ጊዜ ያላት ተስፋ መጽናኛና ጥበቃ ሆኗታል።

አምላክን ማገልገሉ መድኃኒት ሆነለት!

ኦኔስመስ በዘር የሚተላለፍ ኦስቲዎጄነሲስ ኢምፐርፌክታ የተሰኘ የአጥንት በሽታ አለበት። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት አምላክ ቃል የገባቸው ተስፋዎች ያበረታቱት እንዴት ነው?

ከድክመቴ ጥንካሬ ማግኘት

አለተሽከርካሪ ወንበር መንቀሳቀስ የማትችል አንዲት ሴት በአምላክ በመታመኗ ‘ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነ ኃይል’ ማግኘት ችላለች።

ይሖዋ ከሚገባው በላይ አድርጎልኛል

ፌሊክስ አላርኮን በሞተር ብስክሌት በደረሰበት አደጋ ሳቢያ ከአንገቱ በታች ሽባ ቢሆንም ሕይወቱ ትርጉም ያለው ሆኗል።

ወደ አምላክ መቅረቤ ጠቅሞኛል

ሴረ ማይገ ዘጠኝ ዓመት ሲሆናት አካላዊ እድገት ማድረጓን ብታቆምም መንፈሳዊ እድገት ማድረጓን ግን አላቆመችም።

በጣም በሚያስፈልገኝ ወቅት ያገኘሁት ተስፋ

ሚክሎሽ ሌክስ በ20 ዓመቱ በደረሰበት አሳዛኝ አደጋ ምክንያት መንቀሳቀስ የማይችል ሰው ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ እንዲኖረው የረዳው እንዴት ነው?

“ኪንግዝሊ ከቻለ እኔም እችላለሁ!”

በስሪ ላንካ ይኖር የነበረው ኪንግዝሊ ጥቂት ደቂቃዎች የሚወስድ ክፍል ለማቅረብ ሲል ተፈታታኝ ሁኔታዎችን መወጣት አስፈልጎታል።

በዳሰሳ መኖር

ጄምስ ራያን ሲወለድ ጀምሮ መስማት የተሳነው ነው፤ በኋላ ላይ ደግሞ ዓይነ ስውር ሆነ። ሕይወቱ ትርጉም እንዲኖረው የረዳው ምንድን ነው?

መስማት የተሳነኝ መሆኔ ሌሎችን ከማስተማር አላገደኝም

ዋልተር ማርከን መስማት ባይችሉም በይሖዋ አምላክ አገልግሎት አስደሳችና የሚያረካ ሕይወት አሳልፈዋል።

በዓይኖቹ አምላክን የሚያገለግለው ሃይሮ

ከሁሉ የከፋው የሴሬብራል ፖልዚ በሽታ ዓይነት ቢኖርበትም ሃይሮ ደስተኛ ከመሆኑም ሌላ ሕይወቱ ትርጉም ያለው ነው።

እጅ ባይኖረኝም እውነትን አጥብቄ ይዣለሁ

ከባድ የአካል ጉዳት ያጋጠመው አንድ ወጣት በፈጣሪ እንዲያምን የሚያደርገው ምክንያት አገኘ።

“ሕመሜን እያሰብኩ አልብሰለሰልም”

ኢላይዛ ጥንካሬ እንዲኖራት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ሕመሟን እንድትረሳ የረዳት ምንድን ነው?

በአቋሟ ጸንታለች

ሶንግ ሂ ካንግ የ14 ዓመት ልጅ እያለች ለሕይወት አስጊ የሆነ ሕክምና በተሳካ ሁኔታ ሊከናወንላት ችሏል።