በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወላጆቼ ቢፋቱስ? ሁኔታውን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

ወላጆቼ ቢፋቱስ? ሁኔታውን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

ምን ማድረግ ትችላለህ?

 ስለሚያሳስብህ ጉዳይ ሌሎችን አማክር። በፍቺው ምክንያት ምን ያህል እንዳዘንክ ወይም ግራ እንደተጋባህ ለወላጆችህ ንገራቸው። ምናልባት ስለተፈጠረው ነገር ሊያስረዱህ ይችሉ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ ጭንቀትህ ቀለል እንዲልልህ ያደርጋል።

 ወላጆችህ አንተ በፈለግከው ጊዜ ሊረዱህ ካልቻሉ ብስለት ላለው አንድ ጓደኛህ ስሜትህን አውጥተህ ልትነግረው ትችላለህ።—ምሳሌ 17:17

 ከሁሉ በላይ ደግሞ ’ጸሎት ሰሚ’ የሆነው የሰማዩ አባትህ አንተን ለመስማት ምንጊዜም ፈቃደኛ ነው። (መዝሙር 65:2) ’እሱ ስለ አንተ ስለሚያስብ’ የልብህን አውጥተህ ንገረው።—1 ጴጥሮስ 5:7

ማድረግ የሌለብህ ነገር

እጅህ ቢሰበር ሙሉ በሙሉ እስክትድን ድረስ ሥቃይ እንደሚኖርህ ሁሉ የወላጆችህ ፍቺ ያስከተለብህ የስሜት ጉዳትም ለተወሰነ ጊዜ ያሠቃይህ ይሆናል፤ ውሎ አድሮ ግን መዳንህ አይቀርም

 ቂም አትያዝ። የሰባት ዓመት ልጅ ሳለ ወላጆቹ የተለያዩት ዳንኤል እንዲህ ብሏል፦ “ወላጆቼ ራስ ወዳድ ናቸው። ስለ እኛ ስሜትም ሆነ ውሳኔያቸው ስለሚያስከትልብን ነገር ቆም ብለው አላሰቡም።”

 ዳንኤል በንዴት መብከንከኑን ካልተወ ምን ሊያጋጥመው ይችላል?—ፍንጭ፦ ምሳሌ 29:22ን አንብብ።

 ዳንኤል፣ ወላጆቹ ያደረሱበትን በደል ይቅር ማለት ሊከብደው ቢችልም እንኳ ይህን ማድረጉ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?—ፍንጭ፦ ኤፌሶን 4:31, 32ን አንብብ።

 ራስህን የሚጎዳ አካሄድ ከመከተል ተቆጠብ። ዴኒ እንዲህ በማለት ያስታውሳል፦ “ወላጆቼ ከተፋቱ በኋላ ደስታ የራቀኝ ከመሆኑም ሌላ በጭንቀት ተውጬ ነበር። የትምህርት ቤት ውጤቴ ማሽቆልቆል የጀመረ ሲሆን አንድ ዓመት ደገምኩ። ከዚያ በኋላ ደግሞ . . . ክፍል ውስጥ የወጣለት አልምጥ ሆንኩ፤ እንዲሁም ካገኘሁት ሰው ጋር እደባደብ ጀመር።

 ዴኒ ክፍል ውስጥ እንዲህ ዓይነት ባሕርይ ማሳየት የጀመረው ለምን ይመስልሃል? ተደባዳቢ እንዲሆን ያደረገውስ ምን ሊሆን ይችላል?

 በገላትያ 6:7 ላይ የሚገኘው መመሪያ እንደ ዴኒ ዓይነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች ራሳቸውን የሚጎዳ አካሄድ ከመከተል እንዲቆጠቡ ሊረዳቸው የሚችለው እንዴት ነው?

 በስሜት ላይ ከሚደርስ ጉዳት ለማገገም ጊዜ መውሰዱ አይቀርም። ያም ቢሆን እንደ ቀድሞው ነገሮችን በፕሮግራም ማከናወን ስትጀምር ስሜትህ እየተረጋጋ ይመጣል።